free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

ወጣትነት እና መዝናኛዎቻችን

✍ በወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)
Iqra

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ምስጋናና ልቅና ለአለማቱ ጌታ ለአሏህ ይገባው። የአሏህ ሰላምና እዝነት በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በባልደረቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ የውመል ቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።

የወጣትነት ጊዜያችነን ከሚገሉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በሃይማኖታችን ክልክል የሆነ መዝናኛ ነው። ለምሳሌ:- ጫት መቃም ፣ የአልኮል መጠጥ ፣ ናይት ክለብ ፣ ቁማር ፣ ሙዚቃ የተለለያዩ ጌሞች ወ.ዘ.ተ ናቸው። እነዚህ ነገሮች ሐራም የሆኑ የመዝናኛ ማዕከሎች ሲሆኑ ወርቃማውን የወጣትነት ጊዜያችነን ይገላሉ።

በመጀመሪያ ከቅጥ ያለፈ መዝናናት የሚያስፈልገው ችግር በመኖሩ ምክኒያት ነው። ማለቴ አንድ ሰው መንፈሳዊ ችግር ወይም አለመረጋጋት ካለበት መዝነናናት እንዳለበት ያስባል። ሆኖም ብዙ ችግሮች ሲገጥሙት በዛውልክ ብዙ መዝናናትን ይመርጣል።

ሰዎች ለመዝናናት ፣ ለመሳቅ ፣ ለመጫወት ፣ ራሳቸውን ፈታ ለማድረግ ይረዱናል ብለው የሚያስቧቸው የመዝናኛ አይነቶች በሁለት ይከፈላሉ። አንዳንዶቹ በሃይማኖታችን የተከለከሉ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ የተፈቀዱ ናቸው። ለምሳሌ:- ከተከለከሉ የመዝናኛ አይነቶች መካከል አስካሪ መጠጥ ፣ ቁማር ፣ ሙዚቃ ጫት ፣ ሽሻ ፣ ሲጋራ ፣ ሴቶችና ወንዶች ተቀላቅለው የሚዝናኑባቸው ነገሮች ወ.ዘ.ተ ናቸው።

ከእነዚህ ነገሮች ከምንርቅባቸው መንገዶች አንዱ ጠንካራ ኢማን ያለው መሆን ነው። ጠንካራ ኢማን ከሌለን ፣ አሏህን በብቸኝነት የማንገዛ ከሆነ ፣ ያዘዘንን የማንታዘዝ፤ የከለከለንን ነገር የማንከለከል ከሆነና እሱን በማውሳት እስካልተጠመድን ድረስ አዕምሯችን ፣ ቀልባችን ፣ መንፈሳችን ሁሉም ይራባል። ደስታ ሳይሆን ሃዘን በልባችን ይነግሳል። ለዚህም መፍትሄው በመዝናናት ስም ጊዜን ማቃጠልና የአሏህን ህግጋት መጣረስ ሳይሆን አሏህን በብቸኝነት መገዛት ፣ የአሏህ ፍራቻ ያለው መሆን ፣ ልቡን በዚክር ማርጠብ ነው። ይህን ማድረጋችን ሰላምና ደስታን ፣ የአዕምሮ ረፍትና ፅናትን ያጐናፅፈናል። እናም መዝናናት የሚለው ነገር ብዙም አስፈላጊ ሆኖ አናገኘውም። በእርግጥ ሃላል በሆኑ ነገሮች መዝናናት ኢስላም አይከለክልም። እነዚህም እኛን ለማርካት በቂዎች ናቸው።

በህይወታችን ትክክለኛ ደስታ የምናጣጥመው ራሳችነን ለአሏህ ትዕዛዝ ተገዢ ስናደርግ ብቻና ብቻ ነው። ስለዚህ ደስታን የምንፈልግ ከሆነ ራሳችነን በኢማን በተቅዋ በማነፅ ለህይወታችን ህይወት እንስጣት፤ በኢባዳ ተግባሮች እናስውባት፤ ከሃጢያት በመራቅ እንጠብቃት።

እናም ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ አሏህ እሱን በብቸኝነት ተገዝቶው፤ ተቅዋን በልባቸው ዘርተው፤ እሱን ቀን ማታ አውስተው፤ የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ሱና ተከትለው በዱንያም ሆነ በአኺራ ደስታ ከሚጐናፀፉት ባሮቹ ያድርገን። አሚን!!!

768

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ


XtGem Forum catalog